በአፋጣኝ የሚለቀቅ
አድራሻ፡- Cynthia Santana/የኮሙኒኬሽን ስራ አስኪያጅ
206-256-5219
cynthia.santana@seattle.gov
የስራ መደብ መስፈርቶች ቢሮ የ 2025 የዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ መጠንን አስታወቀ
Seattle, WA – (ኦክቶበር 3፣ 2024) –የስራ መደብ መስፈርቶች ቢሮ (OLS፣ Seattle Office of Labor Standards) ከጃንዋሪ 1፣ 2025 ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የሲያትል የመነሻ ደመዎዝ መጠን ላይ ጭማሪ መደረጉን አስታወቀ። ዓመታዊ የዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ ጭማሪ በ Minimum Wage Ordinance (ዝቅተኛ መነሻ የደመወዝ መጠን) መሰረት የተደረገ ነው። የዝቅተኛ መነሻ ደመወዙ የሰራተኛውን የስደተኝነት ሁኔታ ከግምት ውስጥ ሳያስገባ ተፈጻሚ ይሆናል። የዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ ጭማሪ በሲያትል ታኮማ ቤልቪው አካባቢ በሸማቾች ዋጋ መረጃ ጠቋሚ (CPI-W) ላይ ተመስርቶ ያለውን የዋጋ ግሽበት መጠን የሚያንጸባርቅ ይሆናል።
ከጃንዋሪ 1፣ 2025 ጀምሮ፣ ሁሉም ትላልቅ እና አነስተኛ ንግዶች ለሰራተኞች በሰዓት $20.76 ይከፍላሉ።
አነስተኛ ንግዶች ከአሁን በኋላ የዝቅተኛውን መነሻ ደመወዝ ማንኛውም ክፍል ለሠራተኞቻቸው በሚከፈል ቲፕ ወይም የሕክምና ጥቅማጥቅሞች ማሟላት አይችሉም።
Minimum Wage Ordinance በከተማ ውሱኖች ውስጥ ለሚሰሩ ሰራተኞች ዝቅተኛውን የደውወዝ መጠን ይወስናል። የሲያትል የአሁኑ የ2024 ዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ ለትላልቅ አሰሪዎች እና ለሠራተኛው የህክምና ጥቅማጥቅሞች ቢያንስ $2.72 በሰዓት የማይከፍሉ እና/ወይም ሠራተኛው ቢያንስ $2.72 በሰዓት ጒርሻ ለማያገኝባቸው አነስተኛ አሰሪዎች በሰዓት $19.97 ነው። ለሕክምና ጥቅማ ጥቅሞች $2.72/በሰዓት የሚከፍሉ እና/ወይም ሰራተኛው ቢያንስ $2.72/በሰዓት በጉርሻ የሚያገኝባቸው አነስተኛ ቀጣሪዎች አሁን ላይ $17.25/በሰዓት ይከፍላሉ።
OLS የ 2025 የስራ ደረጃዎችን የተመለከቱ መረጃዎችን የያዘ የተሻሻለ የስራ ቦታ ፖስተር ለሁሉም በ Seattle የንግድ ፈቃድ ለሚሰሩ አካላት ይልካል። የስራ ቦታው ፖስተር ቅጂ በእንግሊዘኛ እና በ 33 ሌሎች ቋንቋዎች ተተርጉሞ በቅርቡ የሚገኝ ይሆናል። በ Seattle የሰራተኛ ደረጃዎች ላይ የቅርብ ጊዜ ዝማኔዎችን ለማግኘት ለ OLS ጋዜጣ በ OLS ድረገፅ ላይ ይመዝገቡ።
- እርዳታ ለአሰሪዎች፦ የ Seattle የመነሻ ደመዎዝ እና ሌሎች የስራ ደረጃዎችን በማክበር ረገድ ነጻና ግላዊ እገዛ ለማግኘት፣ ወደ 206-256-5297 ይደውሉ፣ በ business.laborstandards@seattle.gov ወይም እዚህ ጠቅ አድርገው ኦንላይን የመጠየቂያ ቅጽ ይሙሉ።
- እርዳታ ለሰራተኞችና ለሕዝቡ፦ ጥያቄ ለመጠየቅ፣ ቅሬታ ለማቅረብ ወይም መረጃ ለመስጠት፣ በስልክ ቁጥር 206-256-5297 ይደውሉ፣ በ workers.laborstandards@seattle.gov ኢሜይል ይላኩ፣ ወይም የድረገጽ ቅጽ ለመሙላት እዚህ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
####