በአፋጣኝ የሚለቀቅ
አድራሻ፡- Cynthia Santana/የኮሙኒኬሽን ስራ አስኪያጅ
206-256-5219
cynthia.santana@seattle.gov
የስራ ደረጃዎች ጽህፈት ቤት የ 2024 የዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ መጠንን አስታወቀ
Seattle, WA – (ኦክቶበር 16፣ 2023) – የሲያትል የስራ ደረጃዎች ጽህፈት ቤት (OLS, Office of Labor Standards) ከጃንዋሪ 1፣ 2024 ጀምሮ ተፈጻሚ የሚሆን የሲያትል የዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ ጭማሪን አስታውቋል። ዓመታዊ የዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ ጭማሪ በ ዝቅተኛ መነሻ የደመወዝ መጠን (Minimum Wage Ordinance) መሰረት የተደረገ ነው። የዝቅተኛ መነሻ ደመወዙ የሰራተኛውን የስደተኝነት ሁኔታ ከግምት ውስጥ ሳያስገባ ተፈጻሚ ይሆናል። የዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ ጭማሪው የ Seattle Tacoma Bellevue አካባቢ የ Consumer Price Index (CPI፣ የተጠቃሚ ዋጋ ጠቃሚ) ን መሰረት በማድረግ የዋጋ ግሽበት ተመንን ያንጸባርቃል።
- የትልልቅ አሰሪዎች (501 ወይም ከዚያ በላይ ሰራተኞች) የ 2024 ዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ $19.97/ሰዓት ነው።
- ለሰራተኛው የህክምና ጥቅማ ጥቅሞች ቢያንስ $2.72/ሰዓት የማይከፍሉ እና/ወይም ሰራተኛው በቲፕ መልክ ቢያንስ $2.72/ሰዓት የማያገኝባቸው ጥቃቅን አሰሪዎች (500 ወይም ከዚያ በታች ሰራተኞች) የ 2024 ዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ $19.97/ሰዓት ነው።
- ለሰራተኛው የህክምና ጥቅማ ጥቅሞች ቢያንስ $2.72/ሰዓት የሚከፍሉ እና/ወይም ሰራተኛው በቲፕ መልክ ቢያንስ $2.72/ሰዓት የሚያገኝባቸው ጥቃቅን አሰሪዎች የ 2024 ዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ $17.25/ሰዓት ነው።
ከንቲባ Bruce Harrell “ሲያትል የሀገሩ ከፍተኛ የዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ መጠን አለው – ይህም ሰራተኛ ሰዎች የሚኖሩበት እና የሚያድጉበት ከተማን ለመፍጠር ያለውን ግልጽ ቁርጠኝነት ያሳያል።” ብለዋል። “ሰራተኛ ሰዎችን የሚደግፉ ፖሊሲዎችን እና ፕሮግራሞችን ማጠናከር እንቀጥላለን እንዲሁም ሲያትል የሰራተኞች ምሽግ ሆና እንደምትቀጥል እናረጋግጣለን።”
ዝቅተኛ መነሻ የደመወዝ መጠን በከተማ ውሱኖች ውስጥ ለሚሰሩ ሰራተኞች ዝቅተኛውን የደውወዝ መጠን ይወስናል። ለትልልቅ አሰሪዎች እና ለሰራተኛው የህክምና ጥቅማ ጥቅሞች ቢያንስ $2.19/ሰዓት የማይከፍሉ እና/ወይም ሰራተኛው በቲፕ መልክ ቢያንስ $2.19/ሰዓት የማያገኝባቸው ጥቃቅን አሰሪዎች የሲያትል ወቅታዊው የ 2023 ዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ $18.69/ሰዓት ነው። ለሰራተኛው የህክምና ጥቅማ ጥቅሞች ቢያንስ $2.19/ሰዓት የሚከፍሉ እና/ወይም ሰራተኛው በቲፕ መልክ ቢያንስ $2.19/ሰዓት የሚያገኝባቸው ጥቃቅን አሰሪዎችበአሁኑ ሰዓት $16.50/ሰዓት ይከፍላሉ።
OLS የ 2024 የስራ ደረጃዎችን የተመለከቱ መረጃዎችን የያዘ የተሻሻለ የስራ ቦታ ፖስተር ለሁሉም በ Seattle የንግድ ፈቃድ ለሚሰሩ አካላት ይልካል። የስራ ቦታው ፖስተር ቅጂ በእንግሊዘኛ እና በ 29 ሌሎች ቋንቋዎች ተተርጉሞ በቅርቡ የሚገኝ ይሆናል። በ Seattle የሰራተኛ ደረጃዎች ላይ የቅርብ ጊዜ ዝማኔዎችን ለማግኘት ለ OLS ጋዜጣ በ OLS ድረገፅ ላይ ይመዝገቡ።
- እርዳታ ለአሰሪዎች፦ የ Seattle የመነሻ ደመዎዝ እና ሌሎች የስራ ደረጃዎችን በማክበር ረገድ ነጻና ግላዊ እገዛ ለማግኘት፣ ወደ 206-256-5297 ይደውሉ፣ በ business.laborstandards@seattle.gov ወይም እዚህ ጠቅ አድርገው ኦንላይን የመጠየቂያ ቅጽ ይሙሉ።
- እርዳታ ለሰራተኞችና ለሕዝቡ፦ ጥያቄ ለመጠየቅ፣ ቅሬታ ለማቅረብ ወይም መረጃ ለመስጠት፣ በስልክ ቁጥር 206-256-5297 ይደውሉ፣ በ workers.laborstandards@seattle.gov ኢሜይል ይላኩ፣ ወይም የድረገጽ ቅጽ ለመሙላት እዚህ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
####