seattle.gov logoSeattle

  • Services & Information
  • Elected Officials
  • Departments
  • Visiting Seattle
  • News
  • Back toSeattle.gov
  • Seattle.gov
    • Elected Officials
    • Services & Information
      • Animals and Pets
        • Animals and Pets 2
          • Animals and Pets3
      • Arts and Culture
      • Building and Construction
      • Business and Economic Development
      • City Administration
      • City Jobs
      • City Planning and Development
      • Court Services
      • Education, Schools and Learning
      • Environment and Sustainability
      • Grants and Funding
      • Housing, Health and Human Services
      • Neighborhood Services
      • Parks, Recreation and Attractions
      • Police, Fire and Public Safety
      • Streets, Parking and Transportation
      • Technology
      • Utilities
      • Volunteering and Participating
    • Departments
    • Boards & Commissions
    • Visiting Seattle
      • Points of Interest
    • Business in Seattle
    • Skip to main content

    News.seattle.gov

    News from the City of Seattle

    Categories

    የስራ ደረጃዎች ጽህፈት ቤት የ 2024 የዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ መጠንን አስታወቀ

    10/16/2023

    በአፋጣኝ የሚለቀቅ

    አድራሻ፡- Cynthia Santana/የኮሙኒኬሽን ስራ አስኪያጅ
    206-256-5219
    cynthia.santana@seattle.gov

    የስራ ደረጃዎች ጽህፈት ቤት የ 2024 የዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ መጠንን አስታወቀ

    Seattle, WA – (ኦክቶበር 16፣ 2023) – የሲያትል የስራ ደረጃዎች ጽህፈት ቤት (OLS, Office of Labor Standards) ከጃንዋሪ 1፣ 2024 ጀምሮ ተፈጻሚ የሚሆን የሲያትል የዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ ጭማሪን አስታውቋል። ዓመታዊ የዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ ጭማሪ በ ዝቅተኛ መነሻ የደመወዝ መጠን (Minimum Wage Ordinance) መሰረት የተደረገ ነው። የዝቅተኛ መነሻ ደመወዙ የሰራተኛውን የስደተኝነት ሁኔታ ከግምት ውስጥ ሳያስገባ ተፈጻሚ ይሆናል። የዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ ጭማሪው የ Seattle Tacoma Bellevue አካባቢ የ Consumer Price Index (CPI፣ የተጠቃሚ ዋጋ ጠቃሚ) ን መሰረት በማድረግ የዋጋ ግሽበት ተመንን ያንጸባርቃል።

    • የትልልቅ አሰሪዎች (501 ወይም ከዚያ በላይ ሰራተኞች) የ 2024 ዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ $19.97/ሰዓት ነው።
    • ለሰራተኛው የህክምና ጥቅማ ጥቅሞች ቢያንስ $2.72/ሰዓት የማይከፍሉ እና/ወይም ሰራተኛው በቲፕ መልክ ቢያንስ $2.72/ሰዓት የማያገኝባቸው ጥቃቅን አሰሪዎች (500 ወይም ከዚያ በታች ሰራተኞች) የ 2024 ዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ $19.97/ሰዓት ነው።
    • ለሰራተኛው የህክምና ጥቅማ ጥቅሞች ቢያንስ $2.72/ሰዓት የሚከፍሉ እና/ወይም ሰራተኛው በቲፕ መልክ ቢያንስ $2.72/ሰዓት የሚያገኝባቸው ጥቃቅን አሰሪዎች የ 2024 ዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ $17.25/ሰዓት ነው።

    ከንቲባ Bruce Harrell “ሲያትል የሀገሩ ከፍተኛ የዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ መጠን አለው – ይህም ሰራተኛ ሰዎች የሚኖሩበት እና የሚያድጉበት ከተማን ለመፍጠር ያለውን ግልጽ ቁርጠኝነት ያሳያል።” ብለዋል። “ሰራተኛ ሰዎችን የሚደግፉ ፖሊሲዎችን እና ፕሮግራሞችን ማጠናከር እንቀጥላለን እንዲሁም ሲያትል የሰራተኞች ምሽግ ሆና እንደምትቀጥል እናረጋግጣለን።” 

    ዝቅተኛ መነሻ የደመወዝ መጠን በከተማ ውሱኖች ውስጥ ለሚሰሩ ሰራተኞች ዝቅተኛውን የደውወዝ መጠን ይወስናል። ለትልልቅ አሰሪዎች እና ለሰራተኛው የህክምና ጥቅማ ጥቅሞች ቢያንስ $2.19/ሰዓት የማይከፍሉ እና/ወይም ሰራተኛው በቲፕ መልክ ቢያንስ $2.19/ሰዓት የማያገኝባቸው ጥቃቅን አሰሪዎች የሲያትል ወቅታዊው የ 2023 ዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ $18.69/ሰዓት ነው። ለሰራተኛው የህክምና ጥቅማ ጥቅሞች ቢያንስ $2.19/ሰዓት የሚከፍሉ እና/ወይም ሰራተኛው በቲፕ መልክ ቢያንስ $2.19/ሰዓት የሚያገኝባቸው ጥቃቅን አሰሪዎችበአሁኑ ሰዓት $16.50/ሰዓት ይከፍላሉ።

    OLS የ 2024 የስራ ደረጃዎችን የተመለከቱ መረጃዎችን የያዘ የተሻሻለ የስራ ቦታ ፖስተር ለሁሉም በ Seattle የንግድ ፈቃድ ለሚሰሩ አካላት ይልካል። የስራ ቦታው ፖስተር ቅጂ በእንግሊዘኛ እና በ 29 ሌሎች ቋንቋዎች ተተርጉሞ በቅርቡ የሚገኝ ይሆናል። በ Seattle የሰራተኛ ደረጃዎች ላይ የቅርብ ጊዜ ዝማኔዎችን ለማግኘት ለ OLS ጋዜጣ በ OLS ድረገፅ ላይ ይመዝገቡ።  

    • እርዳታ ለአሰሪዎች፦ የ Seattle የመነሻ ደመዎዝ እና ሌሎች የስራ ደረጃዎችን በማክበር ረገድ ነጻና ግላዊ እገዛ ለማግኘት፣ ወደ 206-256-5297 ይደውሉ፣ በ business.laborstandards@seattle.gov ወይም እዚህ ጠቅ አድርገው ኦንላይን የመጠየቂያ ቅጽ ይሙሉ።
    • እርዳታ ለሰራተኞችና ለሕዝቡ፦ ጥያቄ ለመጠየቅ፣ ቅሬታ ለማቅረብ ወይም መረጃ ለመስጠት፣ በስልክ ቁጥር 206-256-5297 ይደውሉ፣ በ workers.laborstandards@seattle.gov ኢሜይል ይላኩ፣ ወይም የድረገጽ ቅጽ ለመሙላት እዚህ ላይ ጠቅ ያድርጉ።

    ####

    Office of Labor Standards, Source: Labor Standards

    Filed Under: News Release, Office of Labor Standards Tagged With: Office of Labor Standards, Source: Labor Standards

    Copyright © 2025 · News Pro Theme on Genesis Framework · WordPress · Log in

    News.seattle.gov
    Entries (RSS)
    Blog Use Notice
    Log in
    ADA Notice
    Notice of Nondiscrimination
    Privacy
    © 1995- 2025 City of Seattle