seattle.gov logoSeattle

  • Services & Information
  • Elected Officials
  • Departments
  • Visiting Seattle
  • News
  • Back toSeattle.gov
  • Seattle.gov
    • Elected Officials
    • Services & Information
      • Animals and Pets
        • Animals and Pets 2
          • Animals and Pets3
      • Arts and Culture
      • Building and Construction
      • Business and Economic Development
      • City Administration
      • City Jobs
      • City Planning and Development
      • Court Services
      • Education, Schools and Learning
      • Environment and Sustainability
      • Grants and Funding
      • Housing, Health and Human Services
      • Neighborhood Services
      • Parks, Recreation and Attractions
      • Police, Fire and Public Safety
      • Streets, Parking and Transportation
      • Technology
      • Utilities
      • Volunteering and Participating
    • Departments
    • Boards & Commissions
    • Visiting Seattle
      • Points of Interest
    • Business in Seattle
    • Skip to main content

    News.seattle.gov

    News from the City of Seattle

    Categories

    Office of Labor Standards የ 2023 የዝቅተኛ መነሻ ደመዎዝ መጠንን አስታወቀ

    10/04/2022

    በአፋጣኝ የሚለቀቅ

    አድራሻ፡- Cynthia Santana/የኮሙኒኬሽን ስራ አስኪያጅ
    206-256-5219
    cynthia.santana@seattle.gov

    Office of Labor Standards የ 2023 የዝቅተኛ መነሻ ደመዎዝ መጠንን አስታወቀ

    Seattle, WA – (ኦክቶበር 4፣ 2022) – የሲያትል Office of Labor Standards (OLS፣ የስራ መደብ መስፈርቶች ቢሮ) ከጃንዋሪ 1/2023 ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የሲያትል የመነሻ ደመዎዝ መጠን ላይ ጭማሪ መደረጉን አስታወቀ። ዓመታዊ የአነስተኛ ደመዎዝ ጭማሪ በ Minimum Wage Ordinance (መነሻ የደመወዝ መጠን) መሰረት የተደረገ ነው። የመነሻ ደመወዙ የሰራተናውን የስደተኝነት ሁኔታ ከግምት ውስጥ ሳያስገባ ተፈጻሚ ይሆናል። የዝቅተኛ መነሻ ደመዎዙ ለ Seattle Tacoma Bremerton በ Consumer Price Index (CPI፣ የተጠቃሚ ዋጋ አመልካች) መሰረ+ት የዋጋ ግሽፈቱን ተመን የሚያንጸባርቅ ነው።

    • ለግዙፍ ቀጣሪዎች (501 ወይም ከዚያ ለሚበልጡ ሰራተኞች) የ 2023 የመነሻ ደመዎዝ መጠን $18.69/በሰዓት ነው።
    • ለሰራተኛው የሕክምና ጥቅማ ጥቅም ቢያንስ $2.19/በሰዓት ለማያዋጡ እና/ወይም ሰራተኛው ቢያንስ $2.19/በሰዓት ጉርሻ ለማያገኝባቸው አነስተኛ ቀጣሪዎች (500 ወይም ከዚያ ለሚያንሱ ሰራተኞች) የ 2023 የመነሻ ደመዎዝ መጠን $18.69/ሰዓት ነው።
    • ለሰራተኛው የሕክምና ጥቅማ ጥቅም ቢያንስ $2.19/በሰዓት ለሚያዋጡ እና/ወይም ሰራተኛው ቢያንስ $2.19/በሰዓት ጉርሻ ለሚያገኝባቸው አነስተኛ ቀጣሪዎች የ 2023 የመነሻ ደመዎዝ መጠን $16.50/በሰዓት ነው።

    Minimum Wage Ordinance በከተማ ውሱኖች ውስጥ ለሚሰሩ ሰራተኞች ዝቅተኛውን የደውወዝ መጠን ይወስናል።  የሲያትል ወቅታዊ ዝቅተኛ የደውወዝ መጠን ለግዙፍ ቀጣሪዎች እና ቢያንስ $1.52/በሰዓት ወደ ሰራተኛው የሕክምና ጥቅማ ጥቅሞች ለማይከፍሉ እና/ወይም ሰራተኛው በጉርሻ መልክ $1.52/በሰዓት ለማያገኝባቸው አነስተና ቀጣሪዎች $17̀.27/በሰዓት ነው። ለሕክምና ጥቅማ ጥቅሞች $1.52/በሰዓት የሚከፍሉ እና/ወይም ሰራተኛው ቢያንስ $1.52/በሰዓት በጉርሻ የሚያገኝባቸው አነስተኛ ቀጣሪዎች አሁን ላይ $15.75/በሰዓት ይከፍላሉ።

    OLS የ 2023 የስራ ደረጃዎችን የተመለከቱ መረጃዎችን የያዘ የተሻሻለ የስራ ቦታ ፖስተር ለሁሉም በ Seattle የንግድ ፈቃድ ለሚሰሩ አካላት ይልካል። ስራ ቦታ ፖስተር ኮፒዎች (በእንግሊዝኛ) ከ OLS ድረገጽ እዚህ ጋር በአሁኑ ሰዓት ለማውረድ ይገኛሉ። ወደ 25 ሌሎች ቋንቋዎች የተተረጎሙ ፖስተሮች በ OLS ቋንቋዎች ድረገጽ ላይ ኦንላይን ይገኛሉ።

    በ Seattle የሰራተኛ ደረጃዎች ላይ የቅርብ ጊዜ ዝማኔዎችን ለማግኘት ለ OLS ጋዜጣ በ OLS ድረገፅ ላይ ይመዝገቡ።  

    • እርዳታ ለአሰሪዎች፦ የ Seattle የመነሻ ደመዎዝ እና ሌሎች የስራ ደረጃዎችን በማክበር ረገድ ነጻና ግላዊ እገዛ ለማግኘት፣ ወደ 206-256-5297 ይደውሉ፣ በ business.laborstandards@seattle.gov ወይም እዚህ ጠቅ አድርገው ኦንላይን የመጠየቂያ ቅጽ ይሙሉ።
    • እርዳታ ለሰራተኞችና ለሕዝቡ:- ጥያቄ ለመጠየቅ፣ ቅሬታ ለማቅረብ ወይም መረጃ ለመስጠት፣ በስልክ ቁጥር 206-256-5297 ይደውሉ፣ በ workers.laborstandards@seattle.gov ኢሜይል ይላኩ፣ ወይም የድረገጽ ቅጽ ለመሙላት እዚህ ላይ ጠቅ ያድርጉ።

    ####

    Office of Labor Standards, Source: Labor Standards

    Filed Under: News Release, Office of Labor Standards Tagged With: Office of Labor Standards, Source: Labor Standards

    Copyright © 2026 · News Pro Theme on Genesis Framework · WordPress · Log in

    News.seattle.gov
    Entries (RSS)
    About Our Digital Properties
    Log in
    Title II: Americans with Disabilities Act
    Title VI: Civil Rights Act
    Privacy
    © 1995- 2026 City of Seattle