seattle.gov logoSeattle

  • Services & Information
  • Elected Officials
  • Departments
  • Visiting Seattle
  • News
  • Back toSeattle.gov
  • Seattle.gov
    • Elected Officials
    • Services & Information
      • Animals and Pets
        • Animals and Pets 2
          • Animals and Pets3
      • Arts and Culture
      • Building and Construction
      • Business and Economic Development
      • City Administration
      • City Jobs
      • City Planning and Development
      • Court Services
      • Education, Schools and Learning
      • Environment and Sustainability
      • Grants and Funding
      • Housing, Health and Human Services
      • Neighborhood Services
      • Parks, Recreation and Attractions
      • Police, Fire and Public Safety
      • Streets, Parking and Transportation
      • Technology
      • Utilities
      • Volunteering and Participating
    • Departments
    • Boards & Commissions
    • Visiting Seattle
      • Points of Interest
    • Business in Seattle
    • Skip to main content

    News.seattle.gov

    News from the City of Seattle

    Categories

    Office of Labor Standards የ 2022 የመነሻ ደመዎዝ መጠንን አስታወቀ ከጃንዋሪ 1፣ 2022 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል – ለሰራተኞች እና ቤት ሰራተኞች በአነስተኛ ደመወዝ እና ለ

    10/18/2021

    ራተኞች በአነስተኛ ደመወዝ እና ለ Transportation Network Company (TNC፣ የትራንስፖርት አውታረ መረብ ኩባንያ) ሾፌር አነስተኛ የካሳ መጠኖች አዲስ አስፈላጊ ማስተካከያዎች

    በአፋጣኝ የሚለቀቅ
    ያነጋግሩ፡- Cynthia Santana/የግንኙነቶች ስራ አስኪያጅ
    206-256-5219
    cynthia.santana@seattle.gov

    Office of Labor Standards የ 2022 የመነሻ ደመዎዝ መጠንን አስታወቀ

    ከጃንዋሪ 1፣ 2022 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል – ለሰራተኞች እና ቤት ሰራተኞች በአነስተኛ ደመወዝ እና ለ Transportation Network Company (TNC፣ የትራንስፖርት አውታረ መረብ ኩባንያ) ሾፌር አነስተኛ የካሳ መጠኖች አዲስ አስፈላጊ ማስተካከያዎች

    Seattle, WA – (ኦክቶበር 18/2021) – Seattle Office of Labor Standards (OLS፣ የሲያትል የስራ መደብ መስፈርቶች ቢሮ) ከጃንዋሪ 1/2022 ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የ Seattle የመነሻ ደመዎዝ መጠን ላይ ጭማሪ እና በ Transportation Network Company (TNC፣ የትራንስፖርት አውታረ መረብ ኩባንያ) አሽከርካሪ አነስተኛ የካሳ መጠኖች ላይ አስፈላጊዎቹ ማስተካከያዎች መደረጋቸውን አስታወቀ።

    የአነስተኛው ደመዎዝ ጭማሪው በ Minimum Wage Ordinance (መነሻ የደመወዝ መጠን) መሰረት የተደረገ ነው። የመነሻ ደመወዙ የስደተኝነት ሁኔታቸውን ከግምት ውስጥ ሳያስገባ Seattle ውስጥ በሚሰሩ ሁሉም ሰራተኞች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል።

    • ለግዙፍ ቀጣሪዎች (501 ወይም ከዚያ ለሚበልጡ ሰራተኞች) የ 2022 የመነሻ ደመዎዝ መጠን $17.27/በሰዓት ነው።
    • ለሰራተኛው የሕክምና ጥቅማ ጥቅም ቢያንስ $1.52/በሰዓት ለማያዋጡ እና/ወይም ሰራተኛው ቢያንስ $1.52/በሰዓት ጉርሻ ለማያገኝባቸው አነስተኛ ቀጣሪዎች (500 ወይም ከዚያ ለሚያንሱ ሰራተኞች) የ 2022 የመነሻ ደመዎዝ መጠን $17.27/ሰዓት ነው።
    • ለሰራተኛው የሕክምና ጥቅማ ጥቅም ቢያንስ $1.52/በሰዓት ለሚያዋጡ እና/ወይም ሰራተኛው ቢያንስ $1.52/በሰዓት ጉርሻ ለሚያገኝባቸው አነስተኛ ቀጣሪዎች የ 2022 የመነሻ ደመዎዝ መጠን $15.75/በሰዓት ነው።

    OLS የ 2022 የስራ ደረጃዎችን የተመለከቱ መረጃዎችን የያዘ የተሻሻለ የስራ ቦታ ፖስተር ለሁሉም በ Seattle የንግድ ፈቃድ ለሚሰሩ አካላት ይልካል። ስራ ቦታ ፖስተር ኮፒዎች (በእንግሊዝኛ) ከ OLS ድረገጽ እዚህ ጋር በአሁኑ ሰዓት ለማውረድ ይገኛሉ። ወደ 19 ሌሎች ቋንቋዎች የተተረጎሙ ፖስተሮች በ OLS ቋንቋዎች ድረገጽ ላይ ኦንላይን ይገኛሉ።

    OLS እንዲሁም በ Seattle ማዘጋጃ ቤት ኮድ 14.33 መሰረት በሚፈለገው መጠን ለ Transportation Network Company (TNC፣ የትራንስፖርት አውታረ መረብ ኩባንያ) አሽከርካሪ አነስተኛ ካሳ በአንድ ማይል መጠን እና ዝቅተኛው የጉዞ መጠንም ያስተዋውቃል። ይህ ህግ በጃንዋሪ 1፣ 2021 ስራ ላይ የዋለ ሲሆን እንደ Uber እና Lyft ያሉ TNCዎች ቢያንስ የ Seattle ትልቁ የአሰሪ ዝቅተኛ ደመወዝ እና ለተመጣጣኝ ወጪዎች ካሳ የሚሆን አነስተኛ የደቂቃ እና የአንድ ማይል ክፍያ እንዲሰጡ ይጠይቃል።  ይህ ህግ የኢሚግሬሽን ሁኔታ ምንም ይሁን ምን በ Seattle ውስጥ የ TNC አገልግሎቶችን የሚያከናውኑ የ TNC አሽከርካሪዎችን ይሸፍናል።

    ከጃንዋሪ 1፣ 2022 ጀምሮ፣ TNC ዎች ትልቁን በአንድ ማይል መጠን $1.38 እና በደቂቃ መጠን $0.59 ወይም ቢያንስ በየጉዞው መጠን ደንበኛው ወይም TNC ጉዞውን ካቋረጠ ጨምሮ በሁሉም ጉዞዎች ላይ $5.17 መክፈል አለባቸው።  OLS አዲሶቹ ተመኖች ጃኑዋሪ 1፣ 2022 ተግባራዊ ከመሆናቸው በፊት ግብዓቶችን ያዘምናል እና ተጨማሪ መረጃ ይሰጣል።

    እንዲሁም ከጃንዋሪ 1፣ 2022 ጀምሮ በ Domestic Workers Ordinance (DWO፣ የቤት ሰራተኞች ደንብ) ሰራተኛው በጣም በሚመቸው ቋንቋ 2022 Model Notice of Rights and Pay Information (2022 የሞዴል የመብቶች ማስታወቂያ እና የክፍያ መረጃ) ን ለሰራተኞቻቸው እንዲያሰራጩ ይበረታታሉ። ይህ የሞዴል ማስታወቂያ በእንግሊዝኛ፣ ስፓኒሽ እና ሌሎች ቋንቋዎች በ OLS ድረገፅ ላይ ይገኛል። OLS በ የቤት ውስጥሰ ራተኞች ደንብ መሰረት ለቤት ሰራተኞች የሚከፈለው ዝቅተኛ ደመወዝ ጭማሪን ለማንፀባረቅ በየዓመቱ ማስታወቂያውን ያዘምናል። እባክዎ የቤት ውስጥ ሰራተኞች ደንብ ድረገጽ በመጠቀም DWO Notice of Rights (የመብቶች ማስታወቂያ) ለማውረድ ይጎብኙ እና በትእዛዙ ላይ ተጨማሪ መረጃ ያግኙ።

    በ Seattle የሰራተኛ ደረጃዎች ላይ የቅርብ ጊዜ ዝማኔዎችን ለማግኘት ለ OLS ጋዜጣ በ OLS ድረገፅ ላይ ይመዝገቡ።  

    • እርዳታ ለአሰሪዎች፦ የ Seattle የመነሻ ደመዎዝ እና ሌሎች የስራ ደረጃዎችን በማክበር ረገድ ነጻና ግላዊ እገዛ ለማግኘት፣ ወደ 206-256-5297 ይደውሉ፣ በ business.laborstandards@seattle.gov ወይም እዚህ ጠቅ አድርገው ኦንላይን የመጠየቂያ ቅጽ ይሙሉ።
    • እርዳታ ለሰራተኞችና ለሕዝቡ:- ጥያቄ ለመጠየቅ፣ ቅሬታ ለማቅረብ ወይም መረጃ ለመስጠት፣ በስልክ ቁጥር 206-256-5297 ይደውሉ፣ በ workers.laborstandards@seattle.gov ኢሜይል ይላኩ፣ ወይም የድረገጽ ቅጽ ለመሙላት እዚህ ላይ ጠቅ ያድርጉ።

    ####

    Office of Labor Standards, Source: Labor Standards

    Filed Under: News Release, Office of Labor Standards Tagged With: Office of Labor Standards, Source: Labor Standards

    Copyright © 2025 · News Pro Theme on Genesis Framework · WordPress · Log in

    News.seattle.gov
    Entries (RSS)
    About Our Digital Properties
    Log in
    Title II: Americans with Disabilities Act
    Title VI: Civil Rights Act
    Privacy
    © 1995- 2025 City of Seattle