ለአፋጣኝ መግለጫ
ያነጋግሩ፡- Cynthia Santana/የኮሙኒኬሽን ስራ አስኪያጅ
206-256-5219 cynthia.santana@seattle.gov
የሲያትል የስራ መደብ መስፈርቶች ቢሮ የ2021 የመነሻ ደመዎዝ መጠን አስታወቀ
Seattle – (ኦክቶበር 6፣ 2020) – የሲያትል የስራ መደብ መስፈርቶች ቢሮ (OLS፣ The Seattle Office of Labor Standards) ከጃኗሪ 1፣ 2021 ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የ Seattle የመነሻ ደመዎዝ መጠን ላይ ጭማሪ መደረጉን አስታወቀ። ጭማሪው በመነሻ ደመዎዝ መጠን ሕግ መሰረት የተደረገ ነው (Minimum Wage Ordinance)። የመነሻ ደመወዙ የስደተኝነት ሁኔታቸውን ከግምት ውስጥ ሳያስገባ Seattle ውስጥ በሚሰሩ ሁሉም ሰራተኞች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል።
- ለግዙፍ ቀጣሪዎች (501 ወይም ከዚያ ለሚበልጡ ሰራተኞች) የ 2021 የመነሻ ደመዎዝ መጠን $16.69/በሰዓት ነው።
- ለሰራተኛው የሕክምና ጥቅማ ጥቅም ቢያንስ $1.69/በሰዓት ለማያዋጡ እና/ወይም ሰራተኛው ቢያንስ $1.69/በሰዓት ጉርሻ ለማያገኝባቸው አነስተኛ ቀጣሪዎች (500 ወይም ከዚያ ለሚያንሱ ሰራተኞች) የ 2021 የመነሻ ደመዎዝ መጠን $16.69/ሰዓት ነው።
- ለሰራተኛው የሕክምና ጥቅማ ጥቅም ቢያንስ $1.69/በሰዓት ለሚያዋጡ እና/ወይም ሰራተኛው ቢያንስ $1.69/በሰዓት ጉርሻ ለሚያገኝባቸው አነስተኛ ቀጣሪዎች የ2021 የመነሻ ደመዎዝ መጠን $15.00/በሰዓት ነው።
OLS የ2021 የስራ ደረጃዎችን የተመለከቱ መረጃዎችን የያዘ የተሻሻለ የስራ ቦታ ፖስተር ለሁሉም በ Seattle የንግድ ፈቃድ ለሚሰሩ አካላት ይልካል። የስራ ቦታ ፖስተር ኮፒዎች (በእንግሊዝኛ) ከOLS ድረ ገጽማውረድ ይቻላል። OLS ፖስተሩን በ19 የተለያዩ ቋንቋዎች የሚያስተረጉም ሲሆን የኦንላይን እና የሕትመት ቅጂዎች መኖራቸውንም በዜና መዋዕሉ አማካይነት ያሳውቃል። እባክዎ ወደ OLS ድረ ገጽ በመግባት ይመዝገቡ።
- እርዳታ ለአሰሪዎች፡ የ Seattle የመነሻ ደመዎዝ እና ሌሎች የስራ ደረጃዎችን በማክበር ረገድ ነጻና ግላዊ እገዛ ለማግኘት፣ ወደ 206-256-5297 ይደውሉ፣ በ business.laborstandards@seattle.gov ኢሜይል ያድርጉ ወይም እዚህ ጠቅ አድርገው ኦንላይን የመጠየቂያ ቅጽ ይሙሉ።
- እርዳታ ለሰራተኞችና ለሕዝቡ:- ጥያቄ ለመጠየቅ፣ ቅሬታ ለማቅረብ ወይም መረጃ ለመስጠት፣ በስልክ ቁጥር 206-256-5297 ይደውሉ፣ በ workers.laborstandards@seattle.gov ኢሜይል ይላኩ፣ የድረ ገጽ ቅጽ ለመሙላት እዚህ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
####